Thursday, 28 November 2013
Wednesday, 27 November 2013
Monday, 25 November 2013
Saturday, 23 November 2013
የአክብሮትና የደስታ መልዕክት ለ41ኛ ኢሕአፓ ምስረታ
ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተነዘሩበት ያለውን ድርጅቱን የማዳከም እርምጃዎችን በአባላቱ ከፍተኛ ንቃት ተቋቁሞ የዘንድሮውን የመጀመሪያ 41 ኛ የምስረታ በአሉን በሰሜን አሜሪካ ያላችሁት የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች በድምቀት ለማክበር በመዘጋጀታችሁ በተለያዩ አካባቢዎች ለምንገኘው አባላትና ደጋፊዎች ምንኛ ኩራት እየሰጠን እንዳለ የድርጅታችንን ማንነት፤ የአባላቱን ፅናትና ጥንካሬ የሚያውቁ የሚገነዘቡት ነውና ደስ ይበላችሁ አብረንም ደስ ይበለን እላለሁ።
በርግጥም 41 አመት በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ ቀላል አመት አይደለም። ድርጅታችን ኢሕአፓ የቆመለት አላማ ሕዝባችን ነፃነቱን በራሱ ትግል እንዲጎናፀፍና ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር በዚህም በመመርኮዝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብሔራዊ ጥቅምና ሀገራዊ አንድነት በእኩልነት ጠብቆና አስጠብቆ ለተተኪው ትውልድ የሚተላለፍበትን ረግረግ ማመቻቸት እንደሆነ ግልፅ ነው። በመሆኑም በነዚህ አመታት የተደረጉትን እልህ አስጨራጭ ትግሎች ወደኋላ ዘር ብለን በሕሊናችን ስንቃኝ የግዴታ በትግሉ ሂደት በተለያዩ ደረጃዎች የተሰዉ አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችንን በዛሬው በድርጅታችን የምስረታ በአል አከባበር ቀን ከአዘቦት ለየት ባለ ሁናቴ ማስታወስ ለኛ ዋና ግዳጅ መሆኑ የሚጠበቅ ነው። ለዚህ ልዩ ምስጢር ኖሮት ሳይሆን ሰማዕታቱን የማያስታውስና ገድላቸውን የማይዘክር የፖለቲካ ድርጅት ተኪ የሌለው ብኩን ሆኖ ስለሚቀር ብቻ ነው። በበኩሌና ይህንን በአል ለማክበር የምትገኙ ሁሉ ኢትዮጵያዊነትና ኢሕአፓነት የዚህ ተቃራኒ ለመሆናቸው ታሪካቸው የሚመሰክርልን እንደሆነ ፅኑ እምነት አለኝ።
በዛሬው እለት ይህንን 41ኛ የምስረታ በአል ቀንን ስናከብር በየቦታው የሚሰነዘሩትንና የተሳሳተ መልስ እንድንሰጥ የሚጋብዙንና ከዋናው የትግል መስመራችን እንድንወጣ የሚያደርጉንን አጓጉል ጥያቄዎች ችላ በማለት ሆኖም ግን ያሳለፍነውን የትግል አመታት በአይነ ሕሊናችን ዞር ብለን በመመልከት፤ የትላንቱን በጥሞና ገምግመን የዛሬን ደግሞ በአርቆ አስተዋይነትና በእርጋታ እያየንና እየፈተንን፤ የነገንም አማትረን መሬት ሳንለቅ ገምተን የት ደርሰናል? ምንስ ማድረግ ይኖርብናል? ምንስ ማድረግ እንችላልን? ምንስ ይጠበቅብናል? የሚሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች በጋራ የምንዳስሥበትም በመሆኑ ይህንን በያለንበት ተግባራዊ እንደምናደርገው ምንም ጥርጥር የለኝም። ተገቢውንም የተግባር መመሪያ እንደምንውስድም እንዲሁ ፅኑ እምነቴ ነው።
ሙሉ ፅሁፉን ሊንኩን በመክፈት ያንብቡ: የአክብሮትና የደስታ መልዕክት ለ41ኛ ኢሕአፓ ምስረታ(ዶር ዘነበ ተሾመ)

Subscribe to:
Posts (Atom)