Wednesday, 18 December 2013

በአንድነታችን እንጽና!!!

ዛሬ በሳኡዲአረብያ ያለውን የክብር ውርደት በእህቶቻችን እና በውንድሞቻችን እየደረሰ ያለውን ግድያ ፤መደፈር እና እንግልት መቼም ቢሆን ከአእምሮአችን የሚጠፋ አይደለም። በየኤምባሲው ጩኽን በቻ የምንተወው ብቻም አይሆንም የጊዜ ጉዳይ እንጂ፧ የተደረገወም የወገን የድረሱልኝ ጥሪ ምላሽም የሚያበረታታ ነው። ይህ አሳፋሪ አሰቃቂ እና አረመኒያዊ ድርጊት በሌላ በኩል በየግላችን ያንገበግበን የነበረውን የባንዲራ ፍቅር የሃገር መቆርቆር የወገን ፍቅር በጋራ እንድንተነፍስ እረድቶናል። በየሆዳችን ያብሰለስለን የነበረውን የሃገር መጥፋት በአንድ ሆነን ተንፍሰነዋል። ያጣነው የመሰለንን አንድነታችንን መኖን በተግባር አይተነዋል
 ከድቶን የመሰለን ወኔያችንን ፈትሸንበታል። የወገን ለወገን ትስስራችንን መተሳሰባችንን ሩህሩህነታችንን እንባችንን መቆጣጠር እያቃተን መርምረንበታል። ለሃገራችን ሲሉ የተሰዉ ሰመአታትን አደራ እንዳልበላን ህያውነታቸውን አረጋግጠንበታል። የህወሃት ሃገር ማጥፋት ዘመቻ ከዚህ እንደማያልፍ አሳይተንበታል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ አሳዛኝ ክስተት ውስጥ ያየነው የተለመደ ቢሆንም በተለይ በዚህ ሰአት መንግስት የወሰደው እርምጃ አሳዛኝ ነው።በተለያየ አለማት ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በሰው ሃገር ሆነው ብሶታቸውን በየአደባባዩ እንዲተነፍሱ ሲፈቀድላቸው ጭራሽ የሙዋቾች ቤተሰቦች ዘመድ እና ጓደኞች አብሮ አደጎች በሚገኙበት በሃገራቸው ድምጻችውን በኤምባሲ በር ለማሰማት ተከልክለዋል ይባስ ብሎ በአደባባይ ተገርፈዋል ታስረዋል። ለኛ ያሳዝናል ያስቆጫል ለወያኔ ቡድን ያሳፍራል።በዚህም ድርጊት የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስት እንደሌለው አረጋገጥን። ያለው ቡድን ከሃገሩ ህዝብ ይልቅ ሀዝቡን ለሚገልለት እንደሚቆም አሳየን። የኢትጵያ ህዝብ ያለመንግስት ተቻችሎ እንደሚኖር ገመትን።መንግስት እና ህዝብ ፍጹም መለያየታቸውን አየንበት። ህዝባችን ጊዜ እና የሚደራጀው ሲያገኝ ምን ሊፈጥር እንደሚችል በአይነ ህሊናችን ሳልንበት።ይህን በዚህ እንይ እንጂ ዛሬ በሳኡዲ የተፈጸመብንን ከዛም በላይ በወገናችን መፈጸም የጀመረው ገና ከመግባቱ ነበር።

በ1984 በበደኖ በአርባጉጉ በግራዋ በሃረር በጎሳ እና በብሄር ስም የተፈጸመው አሰቃቂ ደባ፤dec2012በሰሪ ጎሳ የተፈጸመው ግድያ፤ በጅማ በሃይማኖት ሽፋን የተፈጸመው ሴራ፤በአኝዋክ ብሄር ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በ1993 እና በ1997 የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ በቅርቡ ያየነው በሙስሊሙ ህብረተስብ የተፈጸመው ግድያ አብያተ ከርስትያንን የማጥፋት ዘመቻ በመኪና አደጋ ስም ከጢስ አባይ ገደል የተወረወሩት የአማራ ተፈናቃይ አሳዛኝ ክስተት የተፈጸሙው በዚሁ ገዳያችንን ሳኡዲን አትንኩብኝ ባለው በህወሃት ስርአት ነው።መች ይሄ ብቻ በጫካ ድርድር የባህር በር ያሳጣን፤ አባቶቻችን በደም በአጥንታቸው ያስከበሩትን መሬታችንን ለጎረቤት ሃገሮቻችን እየሰጠ ያለው፤ ይህን ድንግል መሬት እጅግ በረከሰ ዋጋ ለባእዳኖች እየቸበቸበ ያለው፤ ለሃገሬ መከላከያ ሆኜ ሃገሬን አገለግላለሁ በሎ ወደ መከላከያ የሄደውን ወጣት ነፈሱን በሱማሌ አደባባይ እያስጎተተ ለሃያላኖቹ ውለታ ማሰሪያ ያደረገው ይሄው የሃገር አጥፊ ቡድን ነው።በርካታ እህቶቻችን በእስር ቤት የመደፈር ጥቃት እየደረሰባቸው ያለው እውነት በመናግራቸው የህዝብን ብሶት በማሰማታቸው በአሸባሪ ስም እስር ቤት ታጉረው የሚሰቃዩት ርእዩተአለም አሰፋ እስክንድር ነጋ እና አንዱአለም አራጌ ለሃገር ጠቃሚነታቸው እና ውለታቸው ሲታይ በክብር እና በወግ ለንከባከባቸው እና ልንጠቀምባቸው ሲገባ ተቃራኒውን ያገኙት እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጸጋዬ ገብረመድህን ደብተራው ሌሎችም ሰለባ የሆኑት በዚሁ በወያኔ የጥፋት ዘመን ነው። ታዲያ ይህ ሁሉ ስቃይ እና መከራ እያለ ሰሞኑን ያየነው የወገን መቆርቆር እና የሃገር ፍቅር እያለ እንዴት አስችሎን ዝም አልን?? መልሱ በየግላችን የሆናል።አሁን ግን እያሰብን እና እየተወያየን ቁጭ የምንልበት ጊዜ አይደለም።የልቁንም በሃገራችን እና በህዝባችን እየደረሰ ያለውን እንዲሁም ሊመጣ ያለውን መከራ እና የሃገር መጥፋት በማሰብ ሰሞኑን ያሳየነወን የወገን ደራሽነት እና የሃገር ፍቅር ሳይቀዘቅዝ በሃገር ውስጥ ላለው ወገናችንም እንድረስለት ሃገራችንንም ከጥፋት እናድናት ያለአቅሙ በእኛ ዝመታ እና አንድ አለመሆን እድሜውን ያረዘመውን የባእዳን አላማ አስፈጻሚ የሆነውን ውጪው ሲታይ አስፈሪ ውስጡ ግን ባዶ የሆነውን የህወሃት ቡድን እናስውግድ። ይህ እንዲሆን ልዩነታችንን አስወግደን በአንድነት እንጽና፤አላማችን ሃገር ማዳን ይሁን እንደራጅ ህዝባዊ አመጽ ይፋፋም።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!