Saturday, 26 April 2014
ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ
የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡፡
ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ ናትናኤል ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ) እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡
ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ በማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡
ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ስህተትን ማመን ለመጪው ድል ዋስትና ነው
http://articles2u.files.wordpress.com/2014/04/shitetin-marem-ldel-wastina.pdf
ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ
ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ
APRIL 26, 2014 LEAVE A COMMENT

ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡
Source: Ecadforum
Friday, 25 April 2014
የ“ህዳሴው” ግድብ ተጽዕኖ ሌላ አቅጣጫ መያዙ አሳሳቢ ሆኗል
April 25/2014
የአቡነ ማቲያስ የግብጽ ጉብኝት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል

የአቡነ ማቲያስ የግብጽ ጉብኝት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል

ሃያ አምስት በመቶ እንደተጠናቀቀ የሚነገርለት የ“ህዳሴው” ግድብ በኢትዮያና በግብጽ መካከል ከፈጠረው የፖለቲካ ቁርቋሶ በተጨማሪ ወደ ሃይማኖት መንደርም እየዘለቀ ነው፡፡ ዛሬ (አርብ) ግብጽን ለመጎብኘት ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት አቡነ ማቲያስ ከግብጽ በኩል እንዳይመጡ በተላለፈላቸው መልዕክት መሠረት ጉብኝታቸውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡
በግብጽና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የተለያዩ የዜና ዘጋቢዎች እንዳሉት ከሆነ መልዕክቱ ያስተላለፉት የግብጹ ፓትሪያርክ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ ናቸው፡፡ ፓትሪያርኩ ለአቡነ ማቲያስ ባስተላለፉት መልዕክት በበርካታ ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው የአባይ ግድብ የፈጠረው ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ይህንን ጉብኝት ማካሄድ የግብጽን ቤ/ክ “የሚያሳፍር” ይሆናል በሚል ነው ምክራቸውን ለአቡነ ማቲያስ የለገሱት፡፡
ስማቸውን ሳይጠቅሱ መረጃውን ለግብጽ የሚዲያ አካላት የተናገሩት ባለሥልጣን እንደሚሉት ከሆነ ሁለቱ ቤ/ክናት ለረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት ቢኖራቸውም ግድቡን በተመለከተ ይፋዊ ያልሆነ ሽምግልና የማካሄዳቸው ሁኔታ የማያዛልቅ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ሁለቱ ከፍተኛ የቤ/ክ መሪዎች በሚገናኙበት ወቅት ይህ ጉዳይ ሳይነሳ እንደማይታለፍ የታወቀ ነው፡፡
አቡነ ታዋድሮስ “አሳፋሪ” ያሉትን ጉዳይ በዝርዝር አልገለጹትም ሆኖም የግድቡ መሠራት ግብጽን ክፉኛ ያሳሰባት ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በተለያዩ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ስትገባ ከመቆየት አልፋ ኢህአዴግን ለሚቃወሙ የመሣሪያና የመሳሰሉ ዕገዛዎችን ለማድረግ ስትንቀሳቀስ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡
በሃይማኖቱ ዓለም ከፍተኛ ትስስር ያላቸው የግብጽና የኢትዮጵያ ቤ/ክናት ከ“ህዳሴው” ግድብ ጋር በተያያዘ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳቸው የውጥረቱን አሳሳቢነት የሚገልጽ ነው የሚሉ ክፍሎች ግብጽ መረጋጋት ስታገኝ የሚሆነውን ለመተንበይ ያስቸግራል ይላሉ፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ለዕርቅና ሰላም መሥራት በሚገባቸው ጊዜ ከፖለቲካው በላይ መሆን አለመቻላቸው ሹመታቸውም ከዚያው የመነጨ ለመሆኑ ማስረጃ ነው፡፡ አገልግሎታቸውም ከፖለቲካው ሥልጣን በላይ መሆን ያልቻለ መሆኑን በግልጽ ያሳያል በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ያነጋገራቸው ባለሙያ እንደሚሉት የግድቡ ሥራና በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረው ሁኔታ ሁሉንም ሊያሳስብ የሚገባ ነው ይላሉ፡፡ በተለይ ኢህአዴግ የግድቡን ሥራ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ማዋሉ “አስከፊ ነው” ብለዋል፡፡ “አባይን የመገደቡ ጉዳይ አሁን የታሰበ ወይም የተጀመረ አይደለም፤ በንጉሡ ጊዜም ሆነ በደርግ ጊዜ የነበረ ነው፡፡ እኔ የፖለቲካ ተንታኝም ሆነ የታሪክ ምሁር አይደለሁም ነገር ግን በግድቡ ሥራ ላይ ባለኝ ሙያ በከፍተኛ ደረጃ እሳተፋለሁ፡፡ ህወሃት እና ኢህአዴግ ለራሳቸው ርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያነት ሲያውሉትና ሕዝቡን ከንቱ በሆነ አገራዊ ስሜት አስገብተው የራሳቸውን ፖለቲካ ለማራመድ የሚያደርጉትን ሁሉ በየቀኑ በሥራችን ላይ የምናየው አስከፊ ልምምድ ነው፡፡ እኔ የትግራይ ተወላጅ በመሆኔ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቴ አባይ ለዚህ መዋሉ ያስደስተኛል ነገር ግን ኅብረተሰቡ ሲጠይቅ “የግብጽ ደጋፊ ነህ፤ ጸረ-ልማት ነህ ወዘተ” ማለቱ የትም አያደርስም፡፡ በዚህ ላይ ከአገሪቷ ኢኮኖሚ አኳያ የግድቡ ወጪም ሆነ፣ የባለቤትነቱ ጉዳይ እንዲሁም ሌላ በርካታ ጉዳዮች ሊጠየቁ የሚገባቸው ጥያቄዎች ናቸው” ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው የአቡነ ማትያስ የግብጽ ጉብኝት ላሁኑ ተላልፎ የነበረ ሲሆን የአቡነ ታዋድሮስ የመስከረም ወር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውም በተመሳሳይ ምክንያት መሰረዙ ይታወሳል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)