Saturday, 26 April 2014

Ethiopia: Multiple arrests in major crackdown on government critics

http://escondera.blogspot.no/2014/04/ethiopia-multiple-arrests-in-major.html

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ

ጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡፡
ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ ናትናኤል ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ) እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡
ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ በማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡
ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ስህተትን ማመን ለመጪው ድል ዋስትና ነው

http://articles2u.files.wordpress.com/2014/04/shitetin-marem-ldel-wastina.pdf

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ

ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡
Source: Ecadforum

Friday, 25 April 2014

የ“ህዳሴው” ግድብ ተጽዕኖ ሌላ አቅጣጫ መያዙ አሳሳቢ ሆኗል

April 25/2014
የአቡነ ማቲያስ የግብጽ ጉብኝት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል

abay and church
ሃያ አምስት በመቶ እንደተጠናቀቀ የሚነገርለት የ“ህዳሴው” ግድብ በኢትዮያና በግብጽ መካከል ከፈጠረው የፖለቲካ ቁርቋሶ በተጨማሪ ወደ ሃይማኖት መንደርም እየዘለቀ ነው፡፡ ዛሬ (አርብ) ግብጽን ለመጎብኘት ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት አቡነ ማቲያስ ከግብጽ በኩል እንዳይመጡ በተላለፈላቸው መልዕክት መሠረት ጉብኝታቸውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡
በግብጽና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የተለያዩ የዜና ዘጋቢዎች እንዳሉት ከሆነ መልዕክቱ ያስተላለፉት የግብጹ ፓትሪያርክ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ ናቸው፡፡ ፓትሪያርኩ ለአቡነ ማቲያስ ባስተላለፉት መልዕክት በበርካታ ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው የአባይ ግድብ የፈጠረው ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ይህንን ጉብኝት ማካሄድ የግብጽን ቤ/ክ “የሚያሳፍር” ይሆናል በሚል ነው ምክራቸውን ለአቡነ ማቲያስ የለገሱት፡፡
ስማቸውን ሳይጠቅሱ መረጃውን ለግብጽ የሚዲያ አካላት የተናገሩት ባለሥልጣን እንደሚሉት ከሆነ ሁለቱ ቤ/ክናት ለረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት ቢኖራቸውም ግድቡን በተመለከተ ይፋዊ ያልሆነ ሽምግልና የማካሄዳቸው ሁኔታ የማያዛልቅ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ሁለቱ ከፍተኛ የቤ/ክ መሪዎች በሚገናኙበት ወቅት ይህ ጉዳይ ሳይነሳ እንደማይታለፍ የታወቀ ነው፡፡
አቡነ ታዋድሮስ “አሳፋሪ” ያሉትን ጉዳይ በዝርዝር አልገለጹትም ሆኖም የግድቡ መሠራት ግብጽን ክፉኛ ያሳሰባት ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በተለያዩ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ስትገባ ከመቆየት አልፋ ኢህአዴግን ለሚቃወሙ የመሣሪያና የመሳሰሉ ዕገዛዎችን ለማድረግ ስትንቀሳቀስ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡
በሃይማኖቱ ዓለም ከፍተኛ ትስስር ያላቸው የግብጽና የኢትዮጵያ ቤ/ክናት ከ“ህዳሴው” ግድብ ጋር በተያያዘ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳቸው የውጥረቱን አሳሳቢነት የሚገልጽ ነው የሚሉ ክፍሎች ግብጽ መረጋጋት ስታገኝ የሚሆነውን ለመተንበይ ያስቸግራል ይላሉ፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ለዕርቅና ሰላም መሥራት በሚገባቸው ጊዜ ከፖለቲካው በላይ መሆን አለመቻላቸው ሹመታቸውም ከዚያው የመነጨ ለመሆኑ ማስረጃ ነው፡፡ አገልግሎታቸውም ከፖለቲካው ሥልጣን በላይ መሆን ያልቻለ መሆኑን በግልጽ ያሳያል በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ያነጋገራቸው ባለሙያ እንደሚሉት የግድቡ ሥራና በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረው ሁኔታ ሁሉንም ሊያሳስብ የሚገባ ነው ይላሉ፡፡ በተለይ ኢህአዴግ የግድቡን ሥራ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ማዋሉ “አስከፊ ነው” ብለዋል፡፡ “አባይን የመገደቡ ጉዳይ አሁን የታሰበ ወይም የተጀመረ አይደለም፤ በንጉሡ ጊዜም ሆነ በደርግ ጊዜ የነበረ ነው፡፡ እኔ የፖለቲካ ተንታኝም ሆነ የታሪክ ምሁር አይደለሁም ነገር ግን በግድቡ ሥራ ላይ ባለኝ ሙያ በከፍተኛ ደረጃ እሳተፋለሁ፡፡ ህወሃት እና ኢህአዴግ ለራሳቸው ርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያነት ሲያውሉትና ሕዝቡን ከንቱ በሆነ አገራዊ ስሜት አስገብተው የራሳቸውን ፖለቲካ ለማራመድ የሚያደርጉትን ሁሉ በየቀኑ በሥራችን ላይ የምናየው አስከፊ ልምምድ ነው፡፡ እኔ የትግራይ ተወላጅ በመሆኔ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቴ አባይ ለዚህ መዋሉ ያስደስተኛል ነገር ግን ኅብረተሰቡ ሲጠይቅ “የግብጽ ደጋፊ ነህ፤ ጸረ-ልማት ነህ ወዘተ” ማለቱ የትም አያደርስም፡፡ በዚህ ላይ ከአገሪቷ ኢኮኖሚ አኳያ የግድቡ ወጪም ሆነ፣ የባለቤትነቱ ጉዳይ እንዲሁም ሌላ በርካታ ጉዳዮች ሊጠየቁ የሚገባቸው ጥያቄዎች ናቸው” ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው የአቡነ ማትያስ የግብጽ ጉብኝት ላሁኑ ተላልፎ የነበረ ሲሆን የአቡነ ታዋድሮስ የመስከረም ወር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውም በተመሳሳይ ምክንያት መሰረዙ ይታወሳል፡፡

Sunday, 30 March 2014

አሓዝ ቢዯረዯር ሇሕዝብ ምኑ ነው ? ከ አሲምባ ድህረ ገጽ የተገኘ ጽሁፍ


የወያኔ ሟቹ መሪ የአክሱም ሓውሌት ሇወሊይታ ሕዝብ ምኑ ነው ያሇውን አሌረሳንም ። ግብዙ ዘረኛ ኢትዮጵያዊነት የሇም ሲሇን ነበር ። አክሱምም ሼክ ሁሴንም ሊሉበሊም ቁሌቢም ፤ የባላ ታሪካዊ ዋሾዎችም፤ ጭሊአም ቀይ ቀበሮም ሁለ የመሊ ኢትዮጵያ ቅርሶችና መሇያዎች ናቸው ። ይመሇከቱናሌ -- የማይመሇከተን ግን የወያኔ ማፈሪያ ዘረኝነት ነው ። ግድ የላሇን ግን ወያኔ ኤኮኖሚው አዯገ እያሇ የሚዯረድረው የሀሰት አህዝ ነው ።
  • ወያኔና ጭፍሮቹ-አጫፋሪዎቹ በሞሊ የሀገራችን ኤኮኖሚ በየአመቱ ከ 9 በመቶ እስከ 11 በመቲ እያዯገ ነው ብሇው ይሇፍፉብናሌ ። አሀዙንም ይዯረድራለ--ግን ይህ ሁለ ምን ማሇት ነው ። ኤኮኖሚው ይዯግ ይመንዯግ ግን ሇህዝብ ምን ትርጉም አሇው ? እድገቱስ ሀቅ ነው ወይስ ማስተኛና ሀሰት ? የአንድ ሀገር ኤኮኖሚ አዯገ እየተባሇ-ከ 91 ሚሉዮን ሕዝብ ውስጥ አብዛኛው እየተራበ
  •  ከ 80 በመቶው በሊይ ንጹህ የሚጠጣው ውሀ እያጣ፤
  •  99 በመቶ የከተማ ነዋሪው ተገቢ መኖሪያ አጥቶና ብዙ መቶ ሺዎች መንገድ አዳሪ ሆነው፤
  •  ብዙ ሚሉዮኖች ተገቢ መጻዳጃ ቦታ አጥተው፤
  •  95 ከመቶው በሊይ ተገቢ የጤና እንክብካቤ ማግኘት ተስኖት፤
  •  አርሶ አዯሩ በድህነት ማቆ፤
  •  ተትረፈረፈ የተባሇው ቆሳቁስ ሁለ ከአብዛኛው የግዢ አቅዋም በሊይ ሆኖና የኑሮ ውድነት ሰማይ ነክቶ፤
  •  ስራ አጥነት የሚሉዮኑ ዕጣ ፈንታ ሆኖ፤
  •  ቀቢጸ ተስፋ ሀገሪቷን አሽመድምዶ
ባሇበት የ እድገት አሃዝ ትርጉም አሌባና ዋጋ ቢስ መሆኑ ግሌጽ ነው ። ባሇፉት ስርዓት ሕዝብ ሲባሌ ጥቂቶች ነበሩ። ሇሰፊው ሕዝብ ቆምኩ ያሇው አረመኔው የዯርግ አገዛዝም ቢሆን ሕዝብ ሲሌ ራሱን መሆኑ ባካሄዯው ፍጅትና ጭፍጨፋ ግሌጽ አድርጓሌ ። ወያኔ እንኳን ሲጀመርም ላእኔ ህዝብ የራሴ ክሌሌ ሕህዝብ ነው ቢሌም ሇነዚህም ቆሞ ሲጠቅማቸው መቶበመቶአሌታየም--ሁለም ገዢ ክፍሌ የሚያስቀድመው ራሱን ብቻ ነው ። በዚህ በዚያ ቀሇበት መንገድ ተሰራ፤ ሸታታ ኮንዶሚኒየም ሕንጻ ቆመ፤ የከተማ ባቡር ሉገነባ ነው ፤ ግድቡ ግንባታው ጦፈ ወዝተ ቢባሌም በተጨባጭ ከሕዝብ ኑሮ መሻሻሌ አንጻር ሇውጥና መሻሻሌ ሳይሆን መሽቆሌቆሌና ውድቀት ነው ሰፍኖና አፍኖን ያሇው ። እድገት የሚሇካው በሕዝብ ዯህንነትና ብሌጽግና ነው ። የጥቂቶች መንዯሊቀቅ የሚሉዮኖች አይዯሇምና ገዢ ተብየዎች በሙስና ሲጨማሇቁና ሲምነሸነሹ ሕዝብ አሇፈሇት ማሇት የሚቻሌ አይዯሇም ። 95 በመቶ በሊይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገሪቷን ሙስና ጎድቷታሌ ብል ያምናሌ ። ያን ያህሌ ሕዝብ ዯግሞ ኑሮአችን ከበፊቱ ይበሌጥ ተበሊሽቷሌ እያሇ ነው ። በድሀ ሀገሮች ተርታ ኢትዮጵያ ክባሰባቸው አንድቅቅ ናት ። የጤና ጥበቃ ሲነሳም ሚዛኗ ውድቅ ነው ። በሁለም መስክ ሚዛኗ ሲፈረጅ አሳፋሪ ሆኖ ሳሇ ኤኮኖሚዋ በጣም አዯገ ብል ሌፈፋው አሰቃቂ ውሸት ሆኖ ይገኛሌ ። የወያኔ አሃዝ ህዝብን ከረሃብና ስቃይ አያድነውም። ሉያድነውም አይችሌም ። ሇዚህም ነው ወያኔና ዯጋፊዎቹ ኢትዮጵያ ኣዯገች ተመነዯገች ብሇው የሚያቅራሩት ከተራማወናበጃ ውጪ ምንም ትርጉምና ሚዛን የማይኖረው ። ሀቁ ይነገር ከተባሇ ዯግሞ ወያኔ ሲመቸው ሕዝብ ይበዯሊሌ፤ ይሰቃያሌ ። የወያኔ የኤኮኖሚ እድገት የሚጠቅመው ሇወያኔ ብቻ ነው ። የወያኔ ውሸት ነው ። የእድገት መሇኪያው የተዛባ ነው ። የታገሌነውና የምንታገሇው የሕዝብ ሇሆነች ኢትዮጵያ ነውና ጥቂቶች ሲዯሊቸና ሚሉዮኑ ሕዝብ ሲሰቃይ ሀገር አሇፈሊት ማሇትን ሌንቀበሇው ቀርቶ ሌንሰማውም አንፈሌግም ። ባዕዳን የራሳቸው ጥቅም አሊቸውና ቡችልቻቸውን ቢያዳንቁ ሌንዯናገር አይገባም ። ግፋ ቢሌ ቀዳዳቸውን ጨምዳዳ ነው የሚለት ። ከሕዝባችን አንጻር ምንም ያሇፈሌን የሇም፤ እድገት የሇም፤ ድህነት ብሳሰ እንጂ አሌቀነሰም፤ መከራው ከፋ እንጂ ዛቅ በረድ አሊሇም። ሁኔታውን ሇመሇወጥ ትግሌ መፋፋም አሇበት፡፤ ላሊ መሌዕክትን ተጨባጩ ሁኔታ ዔየሰጠን አይዯሇም።
ጸረ ወያኔው ትግል ይፋፋም !

Saturday, 29 March 2014

ምን ማድረግ አለብን? በፍኖተ ዲሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ወቅታዊ ሃተታው



የሚሻለው ጥያቄ ምን ማድረግ እንችላለን የሚለው ነው የሚሉ አሉ --ግን ይሳሳታሉ ። የአቅም ጉዳይ የሁለተኛ ደረጃ ጥያቄ ነው--ከቀደመ ደግሞ አቅምንም ወሳኝና የሚያዳክምም ሊሆን ይችላል ። ለዚህም ነው በየታሪካዊ ወቅቱ ወይም ማጠፊያ ላይ--በተለይም ሁናቴው ሲጠጥር--ምን ማድረግ አለብን ብለን መመርመር የሚገባን ። ማድረግ ያለብንን ስናውቅ የሚቻለን ሁሉ ለዚህ ግብ ልናውል እንችላለን ማለት ነው ። በማይሰራና ትክክል ባልሆነ ግምትና ድምዳሜ ተይዘን ስህተትን እየደገመን የወያኔ ሰለባና መጫወቻ መሆናችንም ያከትማል ማለት ነው ።

ዛሬ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ስንቃኘው ወያኔ በስልጣን ቢቆይም ካለፈው በበለጠ የተከፋፈለበት፤እየተዳከመ ያለበት ሁኔታ ይከሰታል ። የአገዛዙ መሰረት እየተናጋ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም። ከ20 ዓመት በላይ ያየነው አረመኔ ወያኔነት ባሰበት እንጂ አልቀነሰም ። በብዙሀኑና በአገዘዙ መሀል ያለውም ልዩነት ሰፍቷል፤ ቅራኔውም ተባብሷል ። በአንጻሩ የሕዝብ እምቢተኛነት ካለፈው ጊዜ ሲወዳደር በተጠናከረ መልክ እየተከሰተ ነው ። ወደ ሕዝባዊ አመጽ የሚወስደው ጎዳና ተጓዥ እያገኘ ነው ። በዚያው ልክ የሕዝብ ጎራ ድክመቶች ገና በሚገባ አልተወገዱም። የወያኔ ከፋፋይ ሻጥሮች አልከሰሙም። በሕዝብ ጎራ ያሉ ሰርጎ ገቦችና የባዕዳን ቅጥረኞች በሰፊውና በሙሉ ሀይል በሕዝብ ላይ እየተንቀሳቀሱ ናቸው ። የሀገር ወዳድ ሀይሎች ህብረት ለተነገ ወዲያ ቀጥሮን ይዞ ርቋል ። ድርጅቶች ይፈላሉ፤ ለክፍፍሉ አስተዋጾ ያደርጋሉ፤ ይተናሉ ወይም ሌሎችን እያጠቁ ለወያኔ ወፍጮ ባቄላ ያቀርባሉ ። የባዕዳን ሰልፍም አልተቀየረም ። አሜሪካና የአውሮጳ ማህበር የወያኔ ደጋፊዎች ናቸው። ሎሌያቸው እስከሆነ ድረስ ሕዝብን ቢበድል ቢፈጅ ግድ የላቸውም ። መሬት የሸጠላቸው እነ ቻይና ህንድ፤ አረቦችና ሱዳንም ወዳጆቹ ናቸው ። ይህ ሁኔታም የራሱ መልዕክት ምን መደረግ አለበት ለሚለው የሚጠቁመው መልስ ይኖራል ። ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እስካሁን ይህ ነው የሚባል ጽኑ ወዳጅ ገና አልተገኘም ። ደጋፊ ነን ብለው ሊሰየሙ ዝግጁ ናቸው የተባሉት--ሻዕቢያ ተባሉ ግብጽ-- ግባቸው በመሰረቱ ጸረ ኢትዮጵያ መሆኑን አናውቅም የሚሉ ካሉ አድርባይ ወይም የሚታዘንላቸው የፖለቲካ ጅሎች ናቸው ።ለመሆኑ ባለፉት 20 ዓመታት በላይ ሻዕቢያ ረድቶና ደግፎ ያጠናረው የትኛው ትግልና ድርጅት አለ ብለን ብንጠይቅ መልሱ ግልጽ ነው ። ይልቁንስ የነተስፋዬ ጌታቸውና የነኮለኔል ታደሰን አሳዛኝ ዕጣ ያጠኗል ።