Saturday, 29 March 2014

ምን ማድረግ አለብን? በፍኖተ ዲሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ወቅታዊ ሃተታው



የሚሻለው ጥያቄ ምን ማድረግ እንችላለን የሚለው ነው የሚሉ አሉ --ግን ይሳሳታሉ ። የአቅም ጉዳይ የሁለተኛ ደረጃ ጥያቄ ነው--ከቀደመ ደግሞ አቅምንም ወሳኝና የሚያዳክምም ሊሆን ይችላል ። ለዚህም ነው በየታሪካዊ ወቅቱ ወይም ማጠፊያ ላይ--በተለይም ሁናቴው ሲጠጥር--ምን ማድረግ አለብን ብለን መመርመር የሚገባን ። ማድረግ ያለብንን ስናውቅ የሚቻለን ሁሉ ለዚህ ግብ ልናውል እንችላለን ማለት ነው ። በማይሰራና ትክክል ባልሆነ ግምትና ድምዳሜ ተይዘን ስህተትን እየደገመን የወያኔ ሰለባና መጫወቻ መሆናችንም ያከትማል ማለት ነው ።

ዛሬ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ስንቃኘው ወያኔ በስልጣን ቢቆይም ካለፈው በበለጠ የተከፋፈለበት፤እየተዳከመ ያለበት ሁኔታ ይከሰታል ። የአገዛዙ መሰረት እየተናጋ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም። ከ20 ዓመት በላይ ያየነው አረመኔ ወያኔነት ባሰበት እንጂ አልቀነሰም ። በብዙሀኑና በአገዘዙ መሀል ያለውም ልዩነት ሰፍቷል፤ ቅራኔውም ተባብሷል ። በአንጻሩ የሕዝብ እምቢተኛነት ካለፈው ጊዜ ሲወዳደር በተጠናከረ መልክ እየተከሰተ ነው ። ወደ ሕዝባዊ አመጽ የሚወስደው ጎዳና ተጓዥ እያገኘ ነው ። በዚያው ልክ የሕዝብ ጎራ ድክመቶች ገና በሚገባ አልተወገዱም። የወያኔ ከፋፋይ ሻጥሮች አልከሰሙም። በሕዝብ ጎራ ያሉ ሰርጎ ገቦችና የባዕዳን ቅጥረኞች በሰፊውና በሙሉ ሀይል በሕዝብ ላይ እየተንቀሳቀሱ ናቸው ። የሀገር ወዳድ ሀይሎች ህብረት ለተነገ ወዲያ ቀጥሮን ይዞ ርቋል ። ድርጅቶች ይፈላሉ፤ ለክፍፍሉ አስተዋጾ ያደርጋሉ፤ ይተናሉ ወይም ሌሎችን እያጠቁ ለወያኔ ወፍጮ ባቄላ ያቀርባሉ ። የባዕዳን ሰልፍም አልተቀየረም ። አሜሪካና የአውሮጳ ማህበር የወያኔ ደጋፊዎች ናቸው። ሎሌያቸው እስከሆነ ድረስ ሕዝብን ቢበድል ቢፈጅ ግድ የላቸውም ። መሬት የሸጠላቸው እነ ቻይና ህንድ፤ አረቦችና ሱዳንም ወዳጆቹ ናቸው ። ይህ ሁኔታም የራሱ መልዕክት ምን መደረግ አለበት ለሚለው የሚጠቁመው መልስ ይኖራል ። ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እስካሁን ይህ ነው የሚባል ጽኑ ወዳጅ ገና አልተገኘም ። ደጋፊ ነን ብለው ሊሰየሙ ዝግጁ ናቸው የተባሉት--ሻዕቢያ ተባሉ ግብጽ-- ግባቸው በመሰረቱ ጸረ ኢትዮጵያ መሆኑን አናውቅም የሚሉ ካሉ አድርባይ ወይም የሚታዘንላቸው የፖለቲካ ጅሎች ናቸው ።ለመሆኑ ባለፉት 20 ዓመታት በላይ ሻዕቢያ ረድቶና ደግፎ ያጠናረው የትኛው ትግልና ድርጅት አለ ብለን ብንጠይቅ መልሱ ግልጽ ነው ። ይልቁንስ የነተስፋዬ ጌታቸውና የነኮለኔል ታደሰን አሳዛኝ ዕጣ ያጠኗል ።


 ምን ማድረግ አለብን ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ምኞትና ተስፋን ህቅ ብሎ መውሰድ ሳይሆን ሁኔታውን በሚገባ መመርመር ማገናዘብ ይኖርብናል ። ወያኔ ደክሟል ግን ሊወድቅ አንድ ሀሙስ ቀረው ብሎ መመዘኑ ስህተት ነው ። ሊታገሉ የሚጥሩ--በተለይም ብረት አነሳን የሚሉ ቡድኖች አሉ--ግን ወያኔን በጦር ሜዳ ወጥረውት ድል ቀርባለች ማለት ደግሞ ራስን ማታለል ነው ። አሜሪካ የሕዝብን ትግል ይረዳል ይታደጋል ብሎ መገመትም--በአሁኑ ሁኔታ--ራስን ማሞኘት ነው ። ወያኔን ለማስወገድ ከሻዕቢያ መጠጋትም የሚለው እስከዛሬ አልሰራም ። ከግንጠላ ሀይሎች ጋር መለሳለስና ህብረት ማቆምም የሚለው ከንቱ ልፋት ሆኖ ተገኝቷል ። ከሁሉ በላይ ግን የወያኔን መሰረታዊ ይዘትና ጠባይ ለመረዳት ያለመቻሉ ስህተት ነው ምን መደረግ አለበትን ምላሽ አሳጥቶ ትግላችንንም ያጫጫው ። የወያኔ የምርጫ ቧልት ሲካሄድ ቆይቷል ። በ1997ም ወያኔ ቸል ብሎና ተጃጅሎ በምርጫም ተሽንፎ ህዝብን ፈጅቶና ተቃዋሚዎችን በጅምላ አስሮ በጉልበት በስልጣን ሊቆይ ችሏል። ከስህተቱ ተምሮም በሚቀጥለው ምርጫ ከአንድ ወንበር ውጪ ሁሉንም አሸነፍኩ ብሎ እስካሁን ተሰይሟል። ለነገሩ ከዚህ በፊት ነው የወያኔ ስርዓት የአንድ ፓርቲ አገዛ ሆኖ የተገኘው ። በኢትዮጵያ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በድምጽና በምርጫ አለመሆኑን ታሪክ አስተምሮናል።

በአጼውም በደርግም ዘመን ለሽንጎ ወዘተ ምርጫ ተብየዎች ነበሩ ። ውጤታቸው ምስጢር አልነበረም ። በኢትዮጵያ ስልጣን የምትሰርጸው ከአመጽና ከክላሺን አፈሙዝ ብቻ ነው ። ምኞታቸውን ከሀቅ አጋጭተው አለ አመጽና ትጥቃዊ ትግል ለውጥ ይመጣል ወይም ወያኔ ይወድቃል ብለው ዛሬም የሚገምቱ አንድም ባለማወቅ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለወያኔና ለባዕዳን እየረዱና ህዝብን ትጥቅ እያስፈቱ ናቸው ፡፤ አመጽ ወይ የትጥቅ ትግል ከተባለ ምዕራባውያን ይቃውሙናል የሚለው የመርህ ጉዳይ አይደለም--የሚደግፉት አገዛዝ እንዳይወገድባቸው ነው። የሚጠሉትንማ ለመጣል ከሊቢያ እስከ ዩክሬይንና ቬኔዙዌላ በቢሊዮን ደረጃ ገንዘብ አውጥተው አመጽም ወረራም ሲያካሂዱና እያካሄዱም የነበረና አሁንም እያየነው ያለ ነው ።

ወያኔና ሰላም ወይም ዴሞክራሲ ጠላት መሆናቸው ቀደም ሲል እንኳን ባይሆን በ1983 ለሁሉም ዜጋ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ነበር ። ቅጥረኞቹን አሰልፎና በምዕራቦቹ ተረድቶ ትጥቅ ትግል ጊዜው አለፈበት፤ሕዝብ ጦርነት ሰልችቶታልና መሰል ቅብጠራዎችን ቢያሰማም ወያኔ በደም ጎርፍ ላይ ቀዝፎ ዘረኛ መርከቡን ቤት መንግስት ያደረሰ ነበርና የሰላምና ዴሞክራሲን ድምጽ ከቶም የሚያዳምጥ አለመሆኑን አሳይቶ ነበር ። መሞኘትን የመረጡ በዙና ሰለባውም በዛ--ወያኔም ፤ለመጠናከር ጊዜ አገኘ። ዘረኛ አገዛዙን ተደባልቀው ሀገርና ሕዝብን ሊያጠፉ የቋመጡትንም ሳይውል ሳያድር መንጥሮ ገደለ ፤ ለስደት ዳረገ ። ስርዓቱ የአፈናና የዘረኘነት መሆኑን በፍጅትም አሳየ ። የምርጫ ጎዳና የሚወስደው ወደ ለውጥና ደምሞክራሲ ሳይሆን የተጠላውን ወያኔ ማጀብና ማዳመቅ ነው ። የወያኔ የጡት አባቶች አንድ ሳይሆን ሀምሳ ወንበር ልቀቁ ብለው ቢመክሯቸውም የሚገኝ ውጤት የለም፡፤ ከዚህ በፊትም በጣት የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች የፓርላማ አባል ተብለው መሳለቂያ ማፌዣ ከመሆን ያለፈ ውጤት አላስገኙም ፡፤ ወያኔ በሚቆጣጠራት ኢትዮጵያ የስልጣንና የውሳኔ ምንጭ ወይም ማዕከል ፓርላማ ወይም ሽንጎው አይደለም ። እንደ ሌሎች ሀግሮችም ክንቲባና ሀገረ ገዢ መሆንም ለፕሬዚዳንትነት መንገድ እይጠርግም ። ስልጣን ያለችው በተወሰኑ የወያኔ ባለስልጣኖች እጅ ነው ። የስልጣናቸው መሰረት ደግሞ በፖለቲክውና በኤኮኖሚው መስክ ሙሉ ቁጥጥር ማድረግ መቻላቸውና ጦሩንና የአፈና መዋቅሩን መያዛቸው ነው ።ለነገሩ በፓርላምም ነገም ቢሆን ብዙህኑ አባላት ወያኔን ጭፍሮቹ መሆናቸው ከወዲሁ የሚጠበቅ ነው ። ለዚህም ነው መሰረታዊ የዴሞክራሲው ይዘት በማያታይበት በአገዛዙ ጥብቅ ቁጥጥር ስር ምርጫ ብሎ መዳከር ከንቱ የሚሆነው ። የወያኔ ጸረ ዴሞክራሲ ስምሪት ደግሞ ህዝብ እንደሚጠላው በማወቁና የነበረውና ያለው ርዕዮት ድርግሞ ሌላ መንገድ ስለማያሳየው ነው ። ለዚህም ነው ወያኔን በምርጫ ቧልቱ ከማጀብ ይልቅ የምርጫው ህግና ኮሚሽንን በተመለከተ ቀደም ሲልም የተነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዲሟሉ ጠይቆ አሊያም ማዕቀብ ማድረግ ተገቢ ነው የሚባለው ። በህዝብ መብት ላይ በሚያሾፍ ሂደት አንሳተፍም ማለት ራሱ ትግል ነው ። ተገቢውን አቅዋም ይዞም በወያኔ መታገድ የሚያኮራና የሚመሰገን ነው ።
ምን ማድረግ አለብን፡
  • በወያኔ ላይ ምንም ብዥታ ሳይኖረን አገዛዙ በሕዝብ አመጽና ሁለገብ ትግል ለመጣል መነሳት
  •  የተጀመረውን የሕዝብ ተቃውሞ ማጠናከር
  •  ከፋፋይ ሀይሎችን መቋቋም
  •  በተጨባጭ ትግል የባዕዳንን አሰላላፍ ለመቀየር መጣር
  •  ሀቀኛ ሀገር ወዳድ ሀይሎችን መደገፍና እንዲተባባሩ ጫና ማድረግ
  •  ወያኔና መሰሎቹ በብሄረሰብና በሀይማኖት ሊከፋፍሉን የሚጥሩትን መቋቋም
  •  የትግላችን የትኩረት አቅጣጫን አለመሳት
  •  ለወሳኙ ትግል መነሳትና ለ ፍሬ አልባ የወያኔ ዕቅዶች ሰለባ አለመሆን
  •  በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ሕዝብን ትግልና የፖለቲካ እስረኞችን በተመለከት ያልተቋረጠ ቅስቀስና ትግል ማካሄድ
  •  የትግሉ ዋና መድረክ የኢትዮጵያ መሬት መሆኑን መቸም አለመዘንጋት ።
 የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ ከወያኔና ጥቂት ሆዳሞች በስተቀር ያለውን ሁኔታ በተጨባጭ ያውቃል ። ለዚህም ነው ትኩረታችንን በተጨባጩ ትግል ላይ መሆኑ ተገቢ የሚሆነው ። የወያኔን ሥስ ብልት መለየትና ማጥቃት ደግሞ ከድካም ይቀንሳል፡፤ የትኛው የትግል ስልት ነው ወያኔን የሚጎዳው? ወደ ውድቀቱ የሚገፋፋው? ጥያቄው ይህ ነው እንጂ ወያኔና ጌቶቹ ይህ ትግል ፍትሓዊ ነው ያኛው ይጎዳል የሚሉት ሊሆን አይችልም ።

በሁለ ገብ ትግል የወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ እንነሳ!

ውድቀት ለወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!


No comments:

Post a Comment